የኢትዮጵያ ሐገርበቀል እውቀቶች ተቋም የኢትዮጵያ ሐገርበቀል እውቀቶች እንዲጠኑ፣ እንዲታወቁ፣ ስራ ላይ እንዲውሉና ከትውልደ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በሚከተሉት አላማወች ላይ በማትኮር ይሰራል፦
⦁ የሐገርበቀል እውቀቶች ላይ ከተጽኖ ነጻ የሆነ ምርምርና አለማቀፍ ጉባኤወች ማካሄድ
⦁ የተዘረፉ የሐገራችን የእውቀት ሐብቶች እንዲመለሱና ለተገልጋዩ ህዝብ እንዲደርሱ ማድረግ
⦁ ሐገርበቀል ትምህርቶችን የሚማሩ ኢትዮጵያውያንን መደገፍ
⦁ ሐገርበቀል እውቀቶቻችንን ለህዝባችን በተለይም ለወጣቱ ማስተማር
⦁ ሐገርበቀል እውቀቶች በመንግስትና በሚመለከታቸው የሚገባቸውን ትኩረት እንዲያገኙ መስራት
⦁ ሐገርበቀል እውቀቶቻችን በዱሮውና በአዲሱ ትውልድ መካከል፣ እንዲሁም በህብረብዙ ባህሎቻችን መካከል ያለውን ትሥስር ለማጠናከርና ሐገራችንም ለአፍሪካዉያንና ለውጭ ሐገሮችም የራሷን የእውቀት ሐብት እንድታበረከት ለማስቻል
ተግባራችን ከፖለቲካ ፓርቲና ከሃይማኖት ተቋማት ወገንተኝነት የራቀና ሙሉ ሐይሉን የሚያፈሰው ሁሉም የሐገራችን እውቀቶች እንዲታወቁ፣ ስራ ላይ እንዲውሉና ለትውልድ እንዲተላለፉ በመጣር ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
ከላይ የተመለከቱትን አላማወችና የስምምነት ነጥቦች ከግብ ለማድረስ
⦁ በሃገር ቤትና ከኢትዮጵያም ውጭ ያሉ ወገኖች ባሉበት ቦታወች ሁሉ የሐገርበቀል እውቀት አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲኖሯቸው ማድረግ።
⦁ በተራ ቁጥር 1 ከሚቋቋሙት ኮሜቴወች የሚወከሉ አንድ አንድ አባላት ያሉበት አለማቀፍ የሐገርበቀል እውቀቶች ተቋም ኮሜቴ እንዲኖር ማስቻል
⦁ ኮሚቴወቹ የአጭርና የረጅም ጊዜ እቅዶችን አዘጋጅተው ወደተግባር እንዲገቡ ማድረግ
ከእርሰወ ምን ይጠበቃል?
በላይ በተገለጹት ሃሳቦች የሚስማሙ ከሆነና ለዚህ ጥረት የበኩለወትን ለመወጣት ከወሰኑ
⦁ ከላይ በቀረበው ሃሳብ ከተስማሙ ለመገናኘት እንድንችል፣ ስመወትን፣ የስራና የትምህርት ዘርፈወትን፣ ያሉበትን ቦታ፣ ስልክና የኢሜይል አድራሻ በኢሜይላችን ይላኩልን ወይም ይህንን ሊንክ በመጫን በቅጥታ ለአባልነት ይመዝገቡ። 

http://www.instituteofindigenouseducationethiopia.org/create-account/ ወይም አስትያየት ካለዎት ይህንን በመጫን አስተያየትዎትን ይላኩልን።
⦁ ፈቃደኛ ከሆኑ በሚኖሩበት አካባቢ ከሚገኙ ሎሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመገናኘት የሃገርበቀል እውቀቶች አስተባባሪ ቡድን ቢያደራጁና ቢያሳውቁን አብረን ለመስራት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
⦁ በዚህ የተጠቀሱትን አላማወች ከግብ ለማድረስ ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ ቢልኩልኝ በታላቅ አክብሮት የምንቀበል መሆናችንም በትህትና እንገልጳልን።

The Institute for Indigenous Education in Ethiopia (IIEE) is a non-profit organisation established for the study, promotion and protection of indigenous knowledges in Ethiopia. It seeks to address the alarming destruction of indigenous knowledges, languages and cultures of some of the most impoverished societies, communities and groups of the world. In Ethiopia, indigenous knowledges have been undermined due to the adoption of a western education system and the use of English as a medium of instruction from high school through to university. Currently, IIEE supports students in limited number of indigenous schools in Ethiopia through the provision of learning materials. It also facilitates research and publication in the area of indigenous literature, and organises events to raise awareness about the significance of indigenous knowledges and the challenges they face.

In the long term, IIEE envisions the creation of an independent academic institution that will teach students indigenous knowledge from elementary to advanced levels of study. IIEE seeks to promote research in local languages especially in Amharic, the national language of Ethiopia. We also recognise the importance of doing research and publishing in English in order to contribute genuine scholarship to the world regarding Ethiopia’s indigenous knowledges. However, we firmly believe that education and knowledge production should be undertaken using local languages. We hope our endeavours will contribute to dialogue towards changing the education system in favour of indigenous knowledges. We also believe Ethiopians and other researchers interested in critical and indigenous knowledge will benefit from our contributions.

If you have any question,   Please contact us or request your membership.